መክብብ 10:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ደጋሚ ሳይደግምባት እባብ ብትነድፍ ለደጋሚው ትርፍ የለውም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እባብ በድግምት ከመፍዘዙ በፊት ቢነድፍ፣ ለደጋሚው ምንም አይጠቅመውም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እባብ ከነከሰህ በኋላ የእባብ ማፍዘዣ ድግምት ምንም አይጠቅምህም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እባብ ቢነድፍ ባለ መድኀኒትም ባያድን ባለ መድኀኒቱ አይጠቀምም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ደጋሚ ሳይደግምባት እባብ ብትነድፍ ለደጋሚው ትርፍ የለውም። |
ምላስም እንደ እሳት ናት፤ በሰውነት ክፍሎቻችን መካከል የምትገኝ የክፋት ዓለም ናት፤ ሰውነትን ሁሉ ታረክሳለች፤ ደግሞም የፍጥረትን ሩጫ ታቃጥላለች፤ ራሷም በገሃነም ትቃጠላለች።