La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘዳግም 33:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በዚያ የአለቃ እድል ፈንታ ቀርቶአልና የመጀመሪያውን ክፍል ለራሱ መረጠ፥ ወደ ሕዝብ አለቆችም መጣ፥ የጌታንም ጽድቅ፥ ፍርዱንም ከእስራኤል ጋር አደረገ።”

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ለም የሆነውን መሬት ለራሱ መረጠ፤ የአለቃም ድርሻ ለርሱ ተጠብቆለታል። የሕዝቡ መሪዎች በተሰበሰቡ ጊዜ፣ የእግዚአብሔርን የጽድቅ ፈቃድና፣ በእስራኤል ላይ የበየነውን ፍርዱን ፈጸመ።”

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

የመሪነት ድርሻ ስለ ተቀመጠለት፥ ለራሱ የተሻለውን መሬት መረጠ፤ የሕዝብ አለቆች በተሰበሰቡ ጊዜ የእግዚአብሔርን ፈቃድና ሥርዓቱን ለእስራኤል ፈጸመ።”

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በዚያ ከሕ​ዝቡ ገዦች ጋር የተ​ሰ​በ​ሰቡ የአ​ለ​ቆች ምድር እንደ ተከ​ፈ​ለች፥ የመ​ጀ​መ​ሪ​ያ​ውን ፍሬ አየ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ጽድ​ቁን፥ ፍር​ዱ​ንም ከእ​ስ​ራ​ኤል ጋር አደ​ረገ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በዚያ የአለቃ እድል ፈንታ ቀርቶአልና 2 የመጀመሪያውን ክፍል ለራሱ መረጠ፤ 2 ወደ ሕዝብ አለቆችም መጣ፤ 2 የእግዚአብሔርንም ጽድቅ፥ 2 ፍርዱንም ከእስራኤል ጋር አደረገ።

Ver Capítulo



ዘዳግም 33:21
8 Referencias Cruzadas  

የሮቤልም ልጆች ነገድ በየአባቶቻቸው ቤት፥ የጋድም ልጆች ነገድ በየአባቶቻቸው ቤት፥ የምናሴም ነገድ እኩሌታ ርስታቸውን ወርሰዋል።


ሚስቶቻችሁና ልጆቻችሁ ከብቶቻችሁም ሙሴ በዮርዳኖስ ማዶ በሰጣችሁ ምድር ይቀመጡ፤ ነገር ግን እናንተ፥ ጽኑዓን ኃያላን ሁሉ፥ ተሰልፋችሁ በወንድሞቻችሁ ፊት ተሻገሩ፥ እርዱአቸውም፥


በማጠጫው መካከል ካሉት ከቀስተኞች ጩኸት ርቀው፥ በዚያ የጌታን ጽድቅ፥ በእስራኤል ላይ የግዛቱን ጽድቅ ይጫወታሉ፥ ከዚያም በኋላ የጌታ ሕዝብ ወደ በሮች ወረዱ።


በእስራኤል ውስጥ መሪዎች ስለ መሩ፥ ሕዝቡም ነፍሳቸውን በፈቃዳቸው ስለ ሰጡ፥ ጌታን አመስግኑ።