ዘዳግም 32:38 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነዚያ የመሥዋዕታቸውን ስብ የበሉ፥ የመጠጥ መለማመኛቸውንም ወይን የጠጡ? እስቲ እነርሱ ይነሡና ይርዱአችሁ! እስቲ መጠጊያም ይሁኑላችሁ!’” አዲሱ መደበኛ ትርጒም የመሥዋዕታቸውን ሥብ የበሉ፣ የመጠጥ ቍርባናቸውንም የወይን ጠጅ የጠጡ አማልክት ወዴት ናቸው? እስኪ ይነሡና ይርዷችሁ! እስኪ መጠለያ ይስጧችሁ! አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የመሥዋዕታቸውን ስብ የበሉ፥ የወይን ቊርባናቸውን የጠጡ አማልክታቸው ተነሥተው ይርዱአቸው፤ መጠጊያም ይሁኑአቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የመሥዋዕታቸውን ስብ የምትበሉላቸው፥ የመጠጥ ቍርባናችውንም ወይን የምትጠጡላቸው፥ እነርሱ ይነሡ፤ ይርዱአችሁም፤ የሚያድኑአችሁም ይሁኑላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የመሥዋዕታቸውን ስብ የበሉ፥ 2 የመጠጥ ቁርባናቸውንም የወይን ጠጅ የጠጡ? 2 እነርሱ ይነሡ፥ ይርዱአችሁም፥ 2 መጠጊያም ይሁኑላችሁ። |
አምላኮቻቸውን ተከትለው ባመነዘሩና በሠዉላቸው ጊዜ እንዳይጠሩህና ከመሥዋዕታቸው እንዳትበላ፥ በምድሪቱ ከሚኖሩ ሰዎች ጋር ቃል ኪዳን እንዳታደርግ፥
ከካህኑ ከአሮን ዘር ነውር ያለበት ማናቸውም ሰው ለጌታ በእሳት የሚቀርበውን ቁርባን ለማቅረብ አይቅረብ፤ ነውረኛ ነውና የአምላኩን እንጀራ ለማቅረብ አይቅረብ።
ጌታ በእነርሱ ዘንድ የተፈራ ይሆናል፥ የምድርን አማልክት ሁሉ ያጠፋቸዋልና፤ የሕዝቦችም ደሴቶች ሁሉ ላይ የሚኖሩ ሰዎች፥ ሁሉም በያሉበት ሆነው ለእርሱ ይሰግዳሉ።