ዘዳግም 29:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በመካከላቸውም አስጸያፊ ምስሎቻቸውንና የዕንጨትና የድንጋይ፥ የብርና የወርቅ ጣዖቶቻቸውን አይታችኋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በመካከላቸውም አስጸያፊ ምስሎቻቸውንና የዕንጨትና የድንጋይ፣ የብርና የወርቅ ጣዖቶቻቸውን አይታችኋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በመካከላቸው አጸያፊ የሆነውን፥ የእንጨት፥ የድንጋይ፥ የብርና የወርቅ ጣዖቶቻቸውን አይታችኋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ርኩስነታቸውንም፥ በእነርሱም ዘንድ የነበሩትን የእንጨትና የድንጋይ፥ የብርና የወርቅም ጣዖቶቻቸውን አይታችኋልና፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ርኩስነታቸውንም በእነርሱም ዘንድ የነበሩትን የእንጨትና የድንጋይ የብርና የወርቅም ጣዖቶቻቸውን አይታችኋልና፥ |
በተቀመጣችሁባት በግብጽ ምድር እንደሚያደርጉት እናንተም እንዲሁ አታድርጉ፤ እኔም ወደማመጣችሁ ስፍራ ወደ ሆነው በከነዓን ምድር ላይ እንደሚያደርጉት እናንተም እንዲሁ አታድርጉ፤ በሥርዓታቸውም አትሂዱ።
“ጌታ አንተን በአንተም ላይ የምታነግሠውን ንጉሥ አንተና አባቶችህ ወደማታውቁት ሕዝብ ይወስዳችኋል። በዚያም ከእንጨትና ከድንጋይ የተሠሩ ሌሎች አማልክትን ታመልካለህ።