ዘዳግም 29:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን ዛሬ በአምላካችን በጌታ ፊት ከእኛ ጋር በዚህ ከሚቆም ሰው ጋር እንዲሁም ዛሬም ከእኛ ጋር በዚህ ከሌለ ሰው ጋር ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዐብራችሁን በአምላካችን በእግዚአብሔር ፊት እዚህ ከቆማችሁት ጋራ ብቻ ሳይሆን፣ ዛሬ እዚህ ከሌሉትም ጋራ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱ ይህን ቃል ኪዳን የሚገባው ዛሬ በዚህ ስፍራ በፊቱ ከቆምነው ከእኛ ሁሉና ዛሬም ከእኛ ጋር እዚህ ከሌሉት ጋር ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን ዛሬ በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ፊት ከእኛ ጋር በዚህ ከሚቆም ሰው ጋር፥ ዛሬም ከእኛ ጋር በዚህ ከሌለ ሰው ጋር ነው እንጂ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን ዛሬ በአምላካችን በእግዚአብሔር ፊት ከእኛ ጋር በዚህ ከሚቆም ሰው ጋር፥ ዛሬም ከእኛ ጋር በዚህ ከሌለ ሰው ጋር ነው እንጂ፤ |
ፊታቸውንም ወደዚያ አቅንተው፦ ኑ፥ ከቶ በማይረሳ በዘለዓለም ቃል ኪዳን ከጌታ ጋር በአንድነት እንሁን፥ ብለው ወደ ጽዮን የሚወስደውን መንገድ ይጠይቃሉ።
ያላመነ ባል በሚስቱ ተቀድሶአልና፤ ያላመነችም ሚስት በባሏ ተቀድሳለች፤ እንደዚህ ካልሆነ ግን፥ ልጆቻችሁ ርኩሳን ናቸው፤ እንደዚህ ከሆነ ግን የተቀደሱ ናቸው።