ዘዳግም 28:66 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቀንም ሆነ ሌሊት በፍርሀት እንደ ተዋጥህ፥ ሕይወትህ ዋስትና ሳታገኝ፥ ዘወትር በሥጋት ትኖራለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቀንም ሆነ ሌሊት በፍርሀት እንደ ተዋጥህ፣ ሕይወትህ ዋስትና ሳታገኝ፣ ዘወትር በሥጋት ትኖራለህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሕይወትህ ዘወትር በጭንቀት ላይ ይሆናል፤ የመኖር ዋስትናህም የተረጋገጠ ባለመሆኑ ቀንና ሌሊት በፍርሃት ትዋጣለህ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሕይወትህ በዐይኖችህ ፊት የተሰቀለች ትሆናለች፤ ሌሊትና ቀንም ትደነግጣለህ፤ በሕይወትህም አትታመንም፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነፍስህም ታመነታለች፤ ሌሊትና ቀንም ትፈራለህ፥ በሕይወትህም አትታመንም፤ |
በእነዚያ ሕዝቦች መካከል ዕረፍት አታገኝም፤ ለእግርህም ጫማ ማረፊያ ቦታ አይኖርም። በዚያም ጌታ የሚርድ ልብ፥ ፈዛዛ ዐይኖች፥ ደካማም ነፍስ ይሰጥሃል።