የሴትንና የሴት ልጇን ኃፍረተ ሥጋ አትግለጥ፤ የወንድ ልጇን ሴት ልጅ ወይም የሴት ልጇን ሴት ልጅ ኃፍረተ ሥጋዋን ለመግለጥ እርሷን አታግባ፤ ዘመዶች ናቸው፤ ዝሙት ነው።
ዘዳግም 27:23 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “‘ከዐማቱ ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚፈጽም የተረገመ ይሁን!’ “ሕዝቡም ሁሉ፥ ‘አሜን!’ ይበል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ከዐማቱ ጋራ የግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚፈጽም የተረገመ ይሁን።” ሕዝቡም ሁሉ፣ “አሜን!” ይበል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ ‘ከዐማቱ ጋር ግንኙነት የሚፈጽም ወንድ ሁሉ የተረገመ ይሁን!’ “ሕዝቡም ሁሉ ‘አሜን!’ ይበሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ከአማቱ ጋር የሚተኛ ርጉም ይሁን፤ ሕዝቡም ሁሉ አሜን ይላሉ። ከዋርሳው ጋር የሚተኛ ርጉም ይሁን፤ ሕዝቡም ሁሉ አሜን ይሁን ይላሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከአማቱ ጋር የሚተኛ ርጉም ይሁን፤ ሕዝቡም ሁሉ አሜን ይላሉ። |
የሴትንና የሴት ልጇን ኃፍረተ ሥጋ አትግለጥ፤ የወንድ ልጇን ሴት ልጅ ወይም የሴት ልጇን ሴት ልጅ ኃፍረተ ሥጋዋን ለመግለጥ እርሷን አታግባ፤ ዘመዶች ናቸው፤ ዝሙት ነው።