ዘዳግም 26:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ግብፃውያን ግን አንገላቱን፤ አሠቃዩንም፤ በባርነት የጭካኔ ቀንበር ጫኑብን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ግብጻውያን ግን ከባድ ሥራ በማሠራት አንገላቱን፤ አሠቃዩንም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ግብጻውያን ግን አስጨነቁን፤ አዋረዱን፥ ባርያዎችም ሆነን እንድናገለግል አስገደዱን። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ግብፃውያንም ክፉ ነገር አደረጉብን፤ አስጨነቁንም፤ በላያችንም ከባድ ሥራን ጫኑብን፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ግብፃውያንም ክፉ ነገር አደረጉብን፥ አስጨነቁንም፥ በላያችንም ጽኑ ከባድ ሥራን ጫኑብን፤ |
ፈርዖንም፦ “የሚወለደውን ወንድ ልጅ ሁሉ ወደ ዓባይ ወንዝ ጣሉት፥ ሴትን ልጅ ሁሉ ግን በሕይወት እንድትኖር ተዉአት” ብሎ ሕዝቡን ሁሉ አዘዘ።