ዘዳግም 25:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ከግብጽ በወጣህ ጊዜ፥ አማሌቅ በመንገድ በአንተ ላይ ያደረገብህን አስታውስ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከግብጽ በወጣህ ጊዜ፣ አማሌቅ በመንገድ በአንተ ላይ ያደረገብህን አስታውስ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “አንተ ከግብጽ በወጣህበት ጊዜ ዐማሌቃውያን የፈጸሙብህን በደል አትርሳ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ከግብፅ በወጣህ ጊዜ ዐማሌቅ በመንገድ ላይ ያደረገብህን ዐስብ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከግብፅ በወጣችሁ ጊዜ አማሌቅ በመንገድ ላይ ያደረገብህን አስብ፤ |
በለዓምም አማሌቅን አይቶ ምሳሌውን ይመስል ጀመር፥ እንዲህም አለ፦ “የአሕዛብ መጀመሪያ የሆነ አማሌቅ ነበረ፤ ፍጻሜው ግን ወደ ጥፋት የሚያመራ ይሆናል።”