ዘዳግም 23:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከመሣሪያህም ጋር መቆፈሪያ ያዝ፥ በሜዳም በተቀመጥህ ጊዜ ትምስበታለህ፥ ዞረህም ከአንተ የወጣውን በአፈር ትከድነዋለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከትጥቅህም ጋራ መቈፈሪያ ያዝ፤ በምትጸዳዳበት ጊዜ ዐፈር ቈፍረህ በዐይነ ምድርህ ላይ መልስበት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በምትጸዳዱበት ጊዜ እዳሪ ለመቈፈርና መልሶ ለመድፈን የሚያገለግላችሁን አንካሴ ከጦር መሣሪያችሁ ጋር ያዙ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከመሣርያህም ጋር መቈፈሪያ ያዝ፤ ሜዳም በተቀመጥህ ጊዜ ትምስበታለህ፤ ዞረህም ከአንተ የወጣውን በአፈር ትከድነዋለህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከመሣሪያህም ጋር መቈፈሪያ ያዝ፤ በሜዳም በተቀመጥህ ጊዜ ትምስበታለህ፥ ዞረህም ከአንተ የወጣውን በአፈር ትከድነዋለህ። |
ጌታ እግዚአብሔር ሊያድንህ ጠላቶችህንም በእጅህ አሳልፎ ሊሰጥ በሰፈርህ መካከል ይሄዳልና ስለዚህ ነውረኛ ነገር እንዳያይብህ፥ ፊቱንም ከአንተ እንዳይመልስ ሰፈርህ የተቀደስ ይሁን።”