ዘዳግም 22:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን መልካም እንዲሆንልህ ዕድሜህም እንዲረዝም፥ ጫጩቶቹን መውሰድ ትችላለህ፤ እናቲቱን ግን ልቀቃት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጫጩቶቿን መውሰድ ትችላለህ፤ እናቲቱን ግን መልካም እንዲሆንልህና ዕድሜህም እንዲረዝም ልቀቃት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጫጩቶቹን መውሰድ ትችላለህ፤ እናቲቱን ወፍ ግን እንድትበር ልቀቃት፤ ይህን ብታደርግ ሀብታም ሆነህ ለረጅም ዘመን ትኖራለህ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን መልካም ይሆንልህ ዘንድ፥ ዕድሜህም ይረዝም ዘንድ እናቲቱን ልቀቅ፤ ጫጭቶችንም ለአንተ ውሰድ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን መልካም ይሆንልህ ዘንድ ዕድሜህም ይረዝም ዘንድ እናቲቱን ስደድ፥ ጫጩቶችንም ለአንተ ውሰድ። |
ለእናንተ፥ ከእናንተም በኋላ ለልጆቻችሁ መልካም ይሆን ዘንድ፥ ጌታ አምላካችሁ ለዘለዓለም በሚሰጣችሁ ምድር ዕድሜአችሁ ይረዝም ዘንድ፥ እኔ ዛሬ የማዝዛችሁን ሥርዓቱንና ትእዛዙን ጠብቁ።”