በአንቺ በኩል አለፍሁ፥ አየሁሽም፥ እነሆ ጊዜሽ የፍቅር ጊዜ ነበር፥ እኔም መጐናጸፊያዬን በላይሽ ላይ ዘረጋሁና ዕርቃንሽን ሸፈንሁ፥ ማልሁልሽም ከአንቺም ጋር ቃል ኪዳን ገባሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፥ አንቺም የእኔ ሆንሽ።
ዘዳግም 22:30 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ማንም ሰው የአባቱ ሚስት ከሆነችው ከማንኛይቱም ሴት ጋር ግንኙነት በማድረግ አባቱን አያሳፍር።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንድ ሰው የአባቱን ሚስት ማግባት የለበትም፤ የአባቱንም መኝታ አያርክስ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ማንም ሰው የአባቱ ሚስት ከሆነችው ከማንኛይቱም ሴት ጋር ግንኙነት በማድረግ አባቱን አያሳፍር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ማናቸውም ሰው የእንጀራ እናቱን አይውሰድ፤ የአባቱንም ኀፍረት አይግለጥ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ማናቸውም ሰው የአባቱን ሚስት አይውሰድ የአባቱንም፥ ልብስ ጫፍ አይግለጥ። |
በአንቺ በኩል አለፍሁ፥ አየሁሽም፥ እነሆ ጊዜሽ የፍቅር ጊዜ ነበር፥ እኔም መጐናጸፊያዬን በላይሽ ላይ ዘረጋሁና ዕርቃንሽን ሸፈንሁ፥ ማልሁልሽም ከአንቺም ጋር ቃል ኪዳን ገባሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፥ አንቺም የእኔ ሆንሽ።
በእርግጥ በእናንተ መካከል ዝሙት እንዳለ ይወራል፤ የዚያም ዓይነት ዝሙት በአሕዛብስ እንኳ የማይደረግ ነው፤ ይኸውም የአባቱን ሚስት ያገባ ሰው አለ።