ዘዳግም 22:27 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሜዳ ባገኛት ጊዜ የታጨችው ልጃገረድ ብትጮህም የሚደርስላት አልነበረም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምክንያቱም ሰውየው የታጨችውን ልጃገረድ ከከተማ ውጭ ስላገኛትና ብትጮኽም እንኳ ለርዳታ የደረሰላት ማንም ሰው ስላልነበር ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህም የሚሆንበት ምክንያት ያ ሰው ያቺን ለሌላ ሰው ታጭታ የነበረች ልጃገረድ ከከተማ ውጪ በዋለችበት አግኝቶአት ስለ ነበርና ርዳታ ለማግኘት ብትጮኽም የሚደርስላት በማጣትዋ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሜዳ ባገኛት ጊዜ የታጨችው ልጃገረድ ጮኻለችና፥ የሚታደጋትም አልነበረምና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሜዳ ባገኛት ጊዜ የታጨችው ልጃገረድ ጮኻለችና የሚታደጋትም አልነበረምና። |
እርሷ ለሞት የሚያበቃ በደል ስላልፈጸመች በልጃገረዲቱ ላይ ምንም ነገር አይድረስባት፤ ይህ ዓይነቱ ጉዳይ አደጋ ጥሎ ባልንጀራውን ከሚገድል ሰው አድራጎት ጋር የሚመሳሰል ነው።