ሌላ እንዲቀመጥበት አይሠሩም፥ ሌላም እንዲበላው አይተከሉም፤ የሕዝቤ ዕድሜ እንደ ዛፍ ዕድሜ ይሆናልና፥ እኔም የመረጥኋቸው በእጃቸው ሥራ ረጅም ዘመን ደስ ይላቸዋል።
ዘዳግም 20:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወይን ተክሎ ገና ያልበላለት አለን? ወደ ቤቱ ይመለስ፤ ያለበለዚያ በጦርነቱ ላይ ይሞትና ወይኑን ሌላ ሰው ይበላዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወይን ተክሎ ገና ያልበላለት አለን? ወደ ቤቱ ይመለስ፤ አለዚያ በጦርነቱ ላይ ይሞትና ወይኑን ሌላ ሰው ይበላዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወይስ አዲስ የወይን ተክል ተክሎ የመጀመሪያውን ፍሬ ያልሰበሰበ ሰው ይገኛልን? ይህ ከሆነ እርሱ ወደ ቤቱ ይመለስ፤ እርሱ በጦርነት ላይ ቢሞት ወይን ጠጁ ለሌላ ሰው መደሰቻ ይሆናል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወይንም ተክሎ ደስ ያልተሰኘበት ሰው ቢኖር በጦርነት እንዳይሞት ሌላም ሰው ደስ እንዳይሰኝበት ወደ ቤቱ ተመልሶ ይሂድ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወይንም ተክሎ ፍሬውንም ያልበላ ሰው ቢኖር በሰልፍ እንዳይሞት ሌላም ሰው ፍሬውን እንዳይበላ ወደ ቤቱ ተመልሶ ይሂድ። |
ሌላ እንዲቀመጥበት አይሠሩም፥ ሌላም እንዲበላው አይተከሉም፤ የሕዝቤ ዕድሜ እንደ ዛፍ ዕድሜ ይሆናልና፥ እኔም የመረጥኋቸው በእጃቸው ሥራ ረጅም ዘመን ደስ ይላቸዋል።
ሀብታቸው ይዘረፋል፥ ቤቶቻቸውም ይፈርሳሉ፤ ቤቶችንም ይሠራሉ፥ ነገር ግን አይኖሩባቸውም፤ ወይንንም ይተክላሉ፥ የወይን ጠጁን ግን አይጠጡም።
ከቶ በገዛ ገንዘቡ በወታደርነት የሚያገለግል ማን ነው? ወይን ተክሎ ፍሬውን የማይበላ ማን ነው? ወይስ መንጋ እየጠበቀ ከመንጋው ወተት የማይጠጣ ማን ነው?
“አለቆቹም ለሠራዊቱ እንዲህ ይበሉ፤ ‘አዲስ ቤት ሠርቶ ያላስመረቀ አለን? ወደ ቤቱ ተመልሶ ይሂድ፤ ያለበለዚያ በጦርነቱ ላይ ይሞትና ቤቱን የሚያስመርቀው ሌላ ሰው ይሆናል።