የጢሮስ ንጉሥ ኪራም ከዳዊት ጋር ወዳጅነቱን አጽንቶ ቆይቶ ነበር፤ ሰሎሞን በአባቱ በዳዊት እግር መንገሡን በሰማ ጊዜ ወደ እርሱ መልእክተኞቹን ላከ።
ዘዳግም 20:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከተቀበሉህና ደጃቸውን ከከፈቱልህ በከተማዋ ውስጥ ሕዝብ ሁሉ ገባርህ ይሁን፤ ያገልግልህም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከተቀበሉህና ደጃቸውን ከከፈቱልህ፣ በከተማዪቱ ውስጥ ሕዝብ ሁሉ ገባርህ ይሁን፤ ያገልግልህም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የቅጽር በሮቻቸውን ከፍተው እንዲገብሩ የሰላም ድርድርህን ቢቀበሉ በከባድ ሥራ ያገልግሉህ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሰላም ቃልም ቢመልሱልህ ደጅም ቢከፍቱልህ፥ በከተማው ያለው ሕዝብ ሁሉ ይገብሩልህ፤ አገልጋዮችም ይሁኑህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የዕርቅ ቃልም ቢመልሱልህ ደጅም ቢከፍቱልህ፥ በከተማ ውስጥ ያለው ሕዝብ ሁሉ ይገብሩልህ ያገልግሉህም። |
የጢሮስ ንጉሥ ኪራም ከዳዊት ጋር ወዳጅነቱን አጽንቶ ቆይቶ ነበር፤ ሰሎሞን በአባቱ በዳዊት እግር መንገሡን በሰማ ጊዜ ወደ እርሱ መልእክተኞቹን ላከ።
ኤልሳዕም “አይሆንም! እንኳን እነዚህን፥ በሰይፍህና በቀስትህ የማረክኻቸውን ወታደሮች መግደል አይገባህም፤ ይልቅስ የሚበሉትና የሚጠጡትን ምግብ አቅርብላቸውና ወደ ንጉሣቸው ተመልሰው እንዲሄዱ አድርግ” አለው።
በጌዝርም የተቀመጡትን ከነዓናውያንን አላሳደዱአቸውም፥ እስከ ዛሬም ድረስ ከነዓናውያን በኤፍሬም መካከል ተቀምጠዋል፤ እነርሱም የጉልበት ሥራ የሚሠሩ ባሮች ሆነዋል።