ዘዳግም 15:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለባዕድ ያበደርከውን መጠየቅ ትችላለህ፤ ወንድምህ ከአንተ የተበደረውን ማናቸውንም ዕዳ ግን ተወው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለባዕድ ያበደርኸውን መጠየቅ ትችላለህ፤ ወንድምህ ከአንተ የተበደረውን ማንኛውንም ዕዳ ግን ተወው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለውጪ አገር ሰው ያበደርከው ብድር እንዲመለስልህ መጠየቅ ትችላለህ፤ ለማንኛውም እስራኤላዊ ወገንህ ያበደርከው ገንዘብ ግን እንዲመለስልህ መጠየቅ የለብህም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከባዕድ ግን በእርሱ ዘንድ ያለህን ሁሉ መቀበል ትችላለህ፤ በወንድምህ ላይ ያለውን ሁሉ ግን ተውለት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእንግዳ ላይ ያበደርኸውን መፈለግ ትችላለህ፤ በወንድምህ ላይ ያለውን ሁሉ ግን እጅህ ይተወዋል። |
አፈጻጸሙም የሚከተለው ነው፦ አበዳሪ ሁሉ ለባልጀራውም ያበደረውን ይተዋል፥ ጌታ የዕዳ ምሕረት አውጆአልና፥ ያበደረውን ከባልንጀራው ወይም ከወንድሙ ዕዳውን እንዲከፍለው አይጠይቀው።
ለእንግዳው በወለድ አበድረው፥ ነገር ግን ጌታ እግዚአብሔር ልትወርሳት በምትገባባት ምድር በሥራህ ሁሉ እንዲባርክህ ለወንድምህ በወለድ አታበድር።