ቈላስይስ 3:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አባቶች ሆይ! ተስፋ እንዳይቈርጡ ልጆቻችሁን አታበሳጩአቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አባቶች ሆይ፤ ተስፋ እንዳይቈርጡ ልጆቻችሁን አታስመርሯቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወላጆች ሆይ! ተስፋ እንዳይቈርጡ ልጆቻችሁን በቊጣ አታበሳጩአቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አባቶች ሆይ እንዳያዝኑ ልጆቻችሁን አታበሳጩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አባቶች ሆይ፥ ልባቸው እንዳይዝል ልጆቻችሁን አታበሳጩአቸው። |
ባርያዎች ሆይ! ሰውን ደስ ለማሰኘት ስትሉ ለታይታ የምትገዙ አትሁኑ፤ ነገር ግን በቅን ልብ ጌታን እየፈራችሁ ለምድራዊ ጌቶቻችሁ በሁሉ ታዘዙ።