ቈላስይስ 3:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ባሎች ሆይ! ሚስቶቻችሁን ውደዱ፤ የምታማርሯቸውም አትሁኑ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ባሎች ሆይ፤ ሚስቶቻችሁን ውደዱ፤ መራራም አትሁኑባቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ባሎች ሆይ! ሚስቶቻችሁን ውደዱ፤ ጨካኞችም አትሁኑባቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ባሎች ሆይ ሚስቶቻችሁን ውደዱ፤ አትንቀፉአቸውም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ባሎች ሆይ፥ ሚስቶቻችሁን ውደዱ መራራም አትሁኑባቸው። |
በሕይወትህ፥ አንተም ከፀሐይ በታች በምትደክምበት ድካም ይህ እድል ፈንታህ ነውና ከንቱ በሆነ በሕይወትህ ዘመን ሁሉ፥ ከፀሐይ በታች በሰጠህ፥ በከንቱ ዘመንህ ሁሉ፥ ከምትወድዳት ሚስትህ ጋር ደስ ይበልህ።
“ማንም ወደ እኔ የሚመጣ ቢኖር አባቱንና እናቱን ሚስቱንም ልጆቹንም ወንድሞቹንም እኅቶቹንም የራሱን ሕይወት እንኳን ሳይቀር ካልናቀ፥ ደቀ መዝሙሬ ሊሆን አይችልም።
እናንተም ባሎች ሆይ! ጸሎታችሁ እንዳይደናቀፍ ከሚስቶቻችሁ ጋር በመተሳሰብ ኑሩ፤ የሕይወትንም ጸጋ አብረዋችሁ ስለሚወርሱ እንደ ደካማነታቸው ሴቶችን አክብሯቸው።