ከላይ የወረደው እሳት ጫካውንና ተራራውን እንዲያቃጥል የተሰጠውን ትእዛዝ ይፈጽማል፤ እነኚህ ጣዖቶች ግን ከላይ ከተጠቀሱት ጋር አይወዳደሩም፤ በውበትም ሆነ በኃይል ወይም ለሰዎች መልካም ነገር በማድረግ ምንም ችሎታ የላቸውም።