La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




አሞጽ 6:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በውኑ ፈረሶች በዓለታም መሬት ላይ ይጋልባሉን? ወይስ ሰው በበሬዎች በዚያ ላይ ሊያርስ ይችላልን? ነገር ግን እናንተ ፍርድን ወደ ሐሞት፥ የጽድቅንም ፍሬ ወደ እሬት ለወጣችሁ፤

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ፈረሶች በጭንጫ ላይ ይሮጣሉን? ሰውስ እዚያ ላይ በበሬ ያርሳልን? እናንተ ግን ፍትሕን ወደ መርዝነት፣ የጽድቅንም ፍሬ ወደ መራራነት ለወጣችሁ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ፈረሰኛ በቋጥኝ ላይ ሊጋልብ ይችላልን? ገበሬስ በባሕር ላይ በሬ ጠምዶ ማረስ ይችላልን? እናንተ ግን ፍርድን ወደ መርዝ ለወጣችሁ፤ እውነትንም እንደ ሬት መራራ አደረጋችሁ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ፍር​ድን ወደ ቍጣ፥ የእ​ው​ነ​ት​ንም ፍሬ ወደ እሬት ለው​ጣ​ች​ኋ​ልና፥ በውኑ ፈረ​ሶች በጭ​ንጫ ላይ ይሮ​ጣ​ሉን? ወይስ በሬ​ዎች በዚያ ላይ ያር​ሳ​ሉን?

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ፍርድን ወደ ሐሞት፥ የጽድቅንም ፍሬ ወደ እሬት የለወጣችሁ፥ በከንቱም ነገር ደስ የሚላችሁ፦ በኃይላችን ቀንድ የወሰድን አይደለምን? የምትሉ፥ እናንተ ሆይ፥ በውኑ ፈረሶች በጭንጫ ላይ ይጋልባሉን? ወይስ በሬዎች በዚያ ላይ ያርሳሉን?

Ver Capítulo



አሞጽ 6:12
17 Referencias Cruzadas  

አንተ እልከኛ፥ አንገትህን የብረት ጅማት፥ ግንባርህም ናስ እንደሆነ አውቄአለሁ፤


አቤቱ! ዓይንህ እውነትን የምትመለከት አይደለችምን? አንተ ቀሥፈሃቸዋል ነገር ግን አላዘኑም፥ ቀጥቅጠሃቸዋልም ነገር ግን ተግሣጽን ለመቀበል እንቢ አሉ፤ ፊታቸውን ከድንጋይ ይልቅ አጠንክረዋል፤ ለመመለስ እንቢ አሉ።


ክፋትን አርሳችኋል፥ ኃጢአትንም አጭዳችኋል፥ የሐሰትንም ፍሬ በልታችኋል፤ በኃያላንህ ብዛት፥ በመንገድህም ላይ ታምነሃልና።


የማይረባውን ቃላት ተናገሩ፤ በሐሰት መሐላ ቃል ኪዳን አደረጉ፤ ስለዚህ መርዛም አረም በእርሻ ትልሞች ላይ እንደሚበቅል መቅሠፍት በቀለባቸው።


ፈራጅንም ከመካከልዋ አጠፋለሁ፥ ከእርሱም ጋር አለቆችዋን ሁሉ እገድላለሁ፥” ይላል ጌታ።


“በንጉሥ ቅጥሮቻቸውም ግፍንና ቅሚያን የሚያከማቹ ቅን ነገር እንዴት እንደሚደረግ አያውቁም፥” ይላል ጌታ።


ፍርድን ወደ እሬት የምትለውጡ፥ ጽድቅንም በምድር ላይ የምትጥሉ እናንተ ሆይ!


እጆቻቸው ክፉ ለማድረግ የተለማመዱ ናቸው፤ ልዑሉና ፈራጁ ጉቦን ይፈልጋሉ፥ ትልቁም ሰው እንደ ነፍሱ ምኞት ይናገራል፤ እንዲሁም ክፋትን ይጐነጉናሉ።


የጽድቅም ፍሬ ሰላምን ለሚያደርጉ በሰላም ይዘራል።