አሞጽ 2:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያ ቀን በኃያላኑም መካከል ልበ ሙሉው ዕራቁቱን ሆኖ ይሸሻል፥” ይላል ጌታ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጐበዞቹ ተዋጊዎች እንኳ፣ በዚያ ቀን ዕራቍታቸውን ይሸሻሉ፤” ይላል እግዚአብሔር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያን ቀን እጅግ ብርቱ የሆኑ ጦረኞች እንኳ የጦር መሣሪያቸውን እየጣሉ ይሸሻሉ፤” እግዚአብሔር ይህን ተናግሮአል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ልበ ሙሉው ኀይለኛም በኀይሉ አይተማመንም፤ ነገር ግን በዚያ ቀን ዕራቁቱን ሆኖ ይሸሻል” ይላል እግዚአብሔር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በኃያላኑም መካከል ልበ ሙሉው በዚያ ቀን ዕራቁቱን ሆኖ ይሸሻል፥ ይላል እግዚአብሔር። |
በሐጾር ንጉሥ በየቡስና በቄናዊው በሔቤር ጐሣ መካከል መልካም ግንኙነት ስለ ነበር ሲሣራ በእግሩ ሸሽቶ የቄናዊው የሔቤር ሚስት ወደ ሆነችው ወደ ያዔል ድንኳን ሮጠ።