ሐዋርያት ሥራ 8:30 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፊልጶስም ሮጦ የነቢዩን የኢሳይያስን መጽሐፍ ሲያነብ ሰማና “በውኑ የምታነበውን ታስተውለዋለህን?” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፊልጶስም ፈጥኖ ወደ ሠረገላው ሄደ፤ ጃንደረባውም የነቢዩን የኢሳይያስን መጽሐፍ ሲያነብብ ሰምቶ፣ “ለመሆኑ፣ የምታነብበውን ታስተውለዋለህን?” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ፊልጶስ ወደዚያ ሮጦ ሄደና ኢትዮጵያዊው የነቢዩን የኢሳይያስን መጽሐፍ ሲያነብ ሰምቶ “የምታነበው ትርጒሙ ይገባሃልን?” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፊልጶስም ፈጥኖ ደርሶ የነቢዩን የኢሳይያስን መጽሐፍ ሲያነብ ሰማው፤ ፊልጶስም፥ “በውኑ የምታነበውን ታውቀዋለህን?” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፊልጶስም ሮጦ የነቢዩን የኢሳይያስን መጽሐፍ ሲያነብ ሰማና፦ “በውኑ የምታነበውን ታስተውለዋለህን?” አለው። |
ተነሥቶም ሄደ። እነሆም፥ ሕንደኬ የተባለች የኢትዮጵያ ንግሥት ባለሥልጣን የነበረ በገንዘብዋም ሁሉ ኀላፊ አንድ ኢትዮጵያ ጃንደረባ ሊሰግድ ወደ ኢየሩሳሌም መጥቶ ነበር፤
ነገር ግን በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሌሎችን ለማስተማር፥ ዐሥር ሺህ ቃላት በልሳን ከምናገር ይልቅ፥ አምስት ቃላት በአእምሮዬ ብናገር ይሻላል።
ጥበብ የሚያስፈልገው እዚህ ላይ ነው። አእምሮ ያለው የአውሬውን ቍጥር ያስላው፤ የሰው ቍጥር ነውና፤ ቁጥሩም ስድስት መቶ ሥልሳ ስድስት ነው።