በነዚያም ቀኖች፥ ሙሴ ባደገ ጊዜ ወደ ወንድሞቹ ወጣ፥ የሥራቸውንም መከራ ተመለከተ፤ የግብጽም ሰው ከወንድሞቹ አንድ የሆነውን ዕብራዊ ሰው ሲመታ አየ።
ሐዋርያት ሥራ 7:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንዱም ሲበደል አይቶ ረዳው፤ የግብጽን ሰውም መትቶ ለተገፋው ተበቀለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም፣ አንድ ግብጻዊ ከወገኖቹ አንዱን በደል ሲያደርስበት አይቶ ግብጻዊውንም ገደለ፤ ለተገፋው ወገኑም ተበቀለ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከወንድሞቹም አንዱ በአንድ ግብጻዊ ሰው ሲበደልና ሲገፋ አይቶ ረዳው፤ ለተገፋውም በመበቀል ግብጻዊውን መታና ገደለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንድ ግብፃዊም ዕብራዊውን ሲበድለው አገኘና ለዚያ ለተበደለው ረድቶ ግብፃዊውን ገደለው በአሸዋም ቀበረው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንዱም ሲበደል አይቶ ረዳው፥ የግብፅን ሰውም መትቶ ለተገፋው ተበቀለ። |
በነዚያም ቀኖች፥ ሙሴ ባደገ ጊዜ ወደ ወንድሞቹ ወጣ፥ የሥራቸውንም መከራ ተመለከተ፤ የግብጽም ሰው ከወንድሞቹ አንድ የሆነውን ዕብራዊ ሰው ሲመታ አየ።