ሐዋርያት ሥራ 7:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም ወገናችንን ተተንኩሎ ሕፃናትን በሕይወት እንዳይጠብቁ ወደ ውጭ ይጥሉ ዘንድ አድርጎ አባቶቻችንን አስጨነቀ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም ሕዝባችንን በተንኰሉ አስጨነቀ፤ ገና የተወለዱ ሕፃናታቸውም ይሞቱ ዘንድ ወደ ውጭ አውጥተው እንዲጥሏቸው አስገደዳቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አዲሱ ንጉሥ በሕዝባችን ላይ በተንኰል ተነሥቶ አባቶቻችንን ይጨቊናቸው ጀመር፤ ሕፃኖቻቸውም እንዲሞቱና ወደ ውጪ አውጥተው እንዲጥሉአቸው፥ አባቶቻችንን አስገደዳቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም ወገኖቻችንን ተተንኵሎ አባቶቻችንን መከራ አጸናባቸው፤ ወንድ ልጅንም ሁሉ እንዲገድሉ አዘዘ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም ወገናችንን ተተንኵሎ ሕፃናትን በሕይወት እንዳይጠብቁ ወደ ውጭ ይጥሉ ዘንድ አድርጎ አባቶቻችንን አስጨነቀ። |