ሐዋርያት ሥራ 6:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሸንጎም የተቀመጡት ሁሉ ትኩር ብለው ሲመለከቱት እንደ መልአክ ፊት ሆኖ ፊቱን አዩት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሸንጎው ተቀምጠው የነበሩትም ሁሉ እስጢፋኖስን ትኵር ብለው ሲመለከቱት ፊቱ የመልአክ ፊት መስሎ ታያቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህ ጊዜ በሸንጎው የተገኙት ሁሉ እስጢፋኖስን ትኲር ብለው ሲመለከቱት ፊቱ እንደ መልአክ ፊት ሆኖ ታያቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሸንጎም ተቀምጠው የነበሩት ሁሉ ትኩር ብለው ተመለከቱት፤ ፊቱንም እንደ እግዚአብሔር መልአክ ፊት ሆኖ አዩት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሸንጎም የተቀመጡት ሁሉ ትኵር ብለው ሲመለከቱት እንደ መልአክ ፊት ሆኖ ፊቱን አዩት። |
እኔ ግን እላችኋለሁ፥ ወንድሙን የሚቆጣ ሁሉ ፍርድ ይገባዋል፤ ወንድሙን ‘የማያስብ’ የሚለው ሁሉ የሸንጎ ፍርድ ይገባዋል፤ ‘ደደብ’ የሚለውም ሁሉ የገሃነመ እሳት ፍርድ ይገባዋል።
እኛም ሁላችን፥ በመጋረጃ በማይሸፈን ፊት፥ የጌታን ክብር እንደ መስተዋት እያብለጨለጭን፥ የእርሱን መልክ እንድንመስል ከክብር ወደ ክብር እንለወጣለን፥ ይህም መንፈስ ከሚሆን ጌታ የመጣ ነው።