እኔ ግን እላችኋለሁ፥ ወንድሙን የሚቆጣ ሁሉ ፍርድ ይገባዋል፤ ወንድሙን ‘የማያስብ’ የሚለው ሁሉ የሸንጎ ፍርድ ይገባዋል፤ ‘ደደብ’ የሚለውም ሁሉ የገሃነመ እሳት ፍርድ ይገባዋል።
ሐዋርያት ሥራ 5:27 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አምጥተውም በሸንጎ አቆሙአቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሐዋርያትንም አምጥተው በሸንጎው ፊት አቆሟቸው፤ ሊቀ ካህናቱም እንዲህ ሲል ጠየቃቸው፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አምጥተውም በሸንጎው ፊት አቆሙአቸው፤ የካህናት አለቃውም እንዲህ ሲል ጠየቃቸው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አምጥተውም በሸንጎ መካከል አቆሙአቸው፤ ሊቀ ካህናቱም መረመራቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አምጥተውም በሸንጎ አቆሙአቸው። |
እኔ ግን እላችኋለሁ፥ ወንድሙን የሚቆጣ ሁሉ ፍርድ ይገባዋል፤ ወንድሙን ‘የማያስብ’ የሚለው ሁሉ የሸንጎ ፍርድ ይገባዋል፤ ‘ደደብ’ የሚለውም ሁሉ የገሃነመ እሳት ፍርድ ይገባዋል።
በማግሥቱም አይሁድ የከሰሱት በምን ምክንያት እንደሆነ እርግጡን ያውቅ ዘንድ አስቦ ፈታው፤ የካህናት አለቆችና ሸንጎውም ሁሉ ይሰበሰቡ ዘንድ አዘዘ፤ ጳውሎስንም አውርዶ በፊታቸው አቆመው።
በሰሙም ጊዜ ማልደው ወደ መቅደስ ገብተው አስተማሩ። ግን ሊቀ ካህናቱና ከእርሱ ጋር የነበሩት መጥተው ሸንጎውንና የእስራኤልን ልጆች ሽማግሌዎች ሁሉ በአንድነት ጠሩ፤ ያመጡአቸውም ዘንድ ወደ ወኅኒ ላኩ።
ነገር ግን በሕዝብ ሁሉ ዘንድ የከበረ የሕግ መምህር ገማልያል የሚሉት አንድ ፈሪሳዊ በሸንጎ ተነሥቶ ሐዋርያትን ጥቂት ፈቀቅ እንዲያደርጉአቸው አዘዘ፤