ሐዋርያት ሥራ 5:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንድ ሰውም መጥቶ “እነሆ፥ በወኅኒ ያኖራችኋቸው ሰዎች እየቆሙ ሕዝቡንም እያስተማሩ በመቅደስ ናቸው፤” ብሎ አወራላቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚህ ጊዜ አንድ ሰው መጥቶ፣ “እነሆ፤ እስር ቤት ያስገባችኋቸው ሰዎች በቤተ መቅደሱ አደባባይ ቆመው ሕዝቡን እያስተማሩ ናቸው” አላቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህ ጊዜ አንድ ሰው መጣና “በወህኒ ቤት ያስገባችኋቸው ሰዎች እነሆ፥ በቤተ መቅደስ ቆመው ሕዝቡን ያስተምራሉ” ብሎ ነገራቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንድ ሰውም መጥቶ፥ “ያሰራችኋቸው እነዚያ ሰዎች እነሆ፥ በቤተ መቅደስ ውስጥ ናቸው፤ ቆመውም ሕዝቡን ያስተምራሉ” ብሎ ነገራቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንድ ሰውም መጥቶ፦ “እነሆ፥ በወኅኒ ያኖራችኋቸው ሰዎች እየቆሙ ሕዝቡንም እያስተማሩ በመቅደስ ናቸው” ብሎ አወራላቸው። |
“ጌታ እንዲህ ይላል፦ በጌታ ቤት አደባባይ ቁም፥ በጌታም ቤት ውስጥ ለመስገድ ለሚመጡት ለይሁዳ ከተሞች ሁሉ እንድትናገራቸው ያዘዝሁህን ቃላት ሁሉ ተናገር፤ አንዲትም ቃል አትጉድል።