ሐዋርያት ሥራ 5:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በቤተ ክርስቲያን ሁሉና ይህንም በሰሙ ሁሉ ላይ ታላቅ ፍርሃት ሆነ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መላዪቱን ቤተ ክርስቲያንና ይህን የሰሙትን ሁሉ ታላቅ ፍርሀት ያዛቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በቤተ ክርስቲያን ሁሉና ይህን ነገር በሰሙ ሰዎች ሁሉ ላይ ታላቅ ፍርሀት ሆነ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በአብያተ ክርስቲያናትና ይህንም ነገር በሰሙት ሁሉ ላይ ታላቅ ፍርሀት ሆነ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በቤተ ክርስቲያን ሁሉና ይህንም በሰሙ ሁሉ ላይ ታላቅ ፍርሃት ሆነ። |
ለእነርሱም ከማደርገው በጎነት አልመለስም ስል፥ ከእነርሱ ጋር የዘለዓለምን ቃል ኪዳን አደርጋለሁ፤ ከእኔም ዘንድ ፈቀቅ እንዳይሉ መፈራቴን በልባቸው ውስጥ አኖራለሁ።
ይህም በኤፌሶን በሚኖሩት ሁሉ በአይሁድና በግሪክ ሰዎች ዘንድ የታወቀ ሆነ፤ በሁላቸውም ላይ ፍርሃት ወደቀባቸው፤ የጌታም የኢየሱስ ስም ተከበረ፤
በይሁዳም ሁሉና በገሊላ በሰማርያም የነበሩት አብያተ ክርስቲያናት በሰላም ኖሩ፤ ታነጹም፤ በእግዚአብሔርም ፍርሃትና በመንፈስ ቅዱስ መጽናናት እየሄዱ ይበዙ ነበር።
ስለዚህ ወዳጆቼ ሆይ! ሁልጊዜ እንደ ታዘዛችሁ፥ በእናንተ ዘንድ በመኖሬ ብቻ ሳይሆን ይልቁን አሁን ስርቅ ይበልጥ በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ የራሳችሁን መዳን ፈጽሙ፤
ኖኅ ገና ስለማይታየው ነገር ተረድቶ እግዚአብሔርን እየፈራ ቤተ ስዎቹን ለማዳን መርከብን በእምነት አዘጋጀ፤ በዚህም ዓለምን ኰነነ፤ በእምነትም የሚገኘውን ጽድቅ ወራሽ ሆነ።