ሐዋርያት ሥራ 4:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኛስ ያየነውንና የሰማነውን ከመናገር ዝም ማለት አንችልም፤” አሉአቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኛስ ያየነውንና የሰማነውን ከመናገር ወደ ኋላ አንልም።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኛስ ያየነውንና የሰማነውን ከመናገር አንቈጠብም።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኛስ ያየነውንና የሰማነውን ከመናገር ዝም እንል ዘንድ አንችልም።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኛስ ያየነውንና የሰማነውን ከመናገር ዝም ማለት አንችልም” አሉአቸው። |
እኔም፦ “የጌታን ስም አላነሣም፥ ከእንግዲህ ወዲህም በስሙ አልናገርም” ብል፥ በአጥንቶቼ ውስጥ እንደ ገባ እንደሚነድድ እሳት ያለ በልቤ ሆነብኝ፤ ደከምሁ፥ መሸከምም አልቻልሁም።
አንጀቴ! አንጀቴ! ልቤ በጣም ታምሞአል፥ በውስጤም ልቤ ታውኮብኛል፤ ነፍሴ ሆይ! የመለከትን ድምፅና የጦርነትን ሁካታ ሰምተሻልና ዝም ማለት አልችልም።
ስለዚህ በጌታ ቁጣ ተሞልቻለሁ፤ ከመታገሥ ደክሜአለሁ፤ “በጎዳና ባሉ ሕፃናት ላይ በጉልማሶችም ጉባዔ ላይ በአንድነት አፍስሰው፤ ደግሞም ባል ከሚስቱ ጋር ሽማግሌውም በእድሜአቸው ከገፉት ጋር ይያዛሉና።
በለዓምም ባላቅን እንዲህ አለው፦ “እነሆ፥ ወደ አንተ መጥቼአለሁ፤ በውኑ እኔ አሁን አንዳችን ነገር ለመናገር እችላለሁን? እግዚአብሔር በአፌ የሚያድርገውን ቃል እርሱን እናገራለሁ።”
ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በወረደ ጊዜ ኃይልን ትቀበላላችሁ፤ በኢየሩሳሌምም በይሁዳም ሁሉ በሰማርያም እስከ ምድር ዳርም ድረስ ምስክሮቼ ትሆናላችሁ፤” አለ።