ሐዋርያት ሥራ 27:32 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ያንጊዜ ወታደሮቹ የታንኳይቱን ገመድ ቆርጠው ትወድቅ ዘንድ ተዉአት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚህ ጊዜ ወታደሮቹ ገመዶቹን ቈርጠው ትንሿ ጀልባ ባሕሩ ላይ ተንሳፍፋ እንድትቀር ለቀቋት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ወታደሮቹ ጀልባውን የያዘውን ገመድ ቈረጡና እንድትንሳፈፍ ተዉአት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወታደሮችም ወዲያውኑ ተነሥተው የታንኳዪቱን ገመድ ቈርጠው ትወድቅ ዘንድ ተዉአት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ያን ጊዜ ወታደሮቹ የታንኳይቱን ገመድ ቈርጠው ትወድቅ ዘንድ ተዉአት። |
ቀንም ሲነጋ ጳውሎስ ምግብ ይበሉ ዘንድ ሁሉን ይለምን ነበር፤ እንዲህም አላቸው “እየጠበቃችሁ ምንም ሳትቀበሉ ጦማችሁን ከሰነበታችሁ ዛሬ ዐሥራ አራተኛ ቀናችሁ ነው።