ሐዋርያት ሥራ 27:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቄዳ በሚሉአትም ደሴት በተተገንን ጊዜ ታንኳይቱን ለመግታት በጭንቅ ቻልን፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቄዳ የተባለችውን ትንሽ ደሴት ተገን አድርገን በማለፍ፣ የመርከቧን ሕይወት አድን ጀልባ በብዙ ድካም ለማትረፍ ቻልን፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቄዳ የተባለችውን ደሴት ተገን አድርገን ስንጓዝ በታላቅ ችግር የመርከቡን ጀልባ ይዘን በቊጥጥራችን ሥር ለማድረግ ቻልን። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዚህም በኋላ ቄዳ ወደምትባል ደሴት እስክንገባ ድረስ ነፋሱ ነፈሰ፤ በጭንቅም ታንኳችንን ለመግታት ቻልን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቄዳ በሚሉአትም ደሴት በተተገንን ጊዜ ታንኳይቱን ለመግዛት በጭንቅ ቻልን፤ |
ወደ ላይም ካወጡአት በኋላ መርከቡን በገመድ አስታጥቀው አጸኑ፤ ስርቲስም ወደሚሉት ወደ አሸዋ እንዳይወድቁ ፈርተው ሸራውን አውርደው እንዲሁ ተነዱ።