ሐዋርያት ሥራ 25:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያን ጊዜ ፊስጦስ ከአማካሪዎቹ ጋር ተማክሮ “ወደ ቄሣር ይግባኝ ብለሃል፤ ወደ ቄሣር ትሄዳለህ፤” ብሎ መለሰለት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፊስጦስ ከመማክርቱ ጋራ ከተመካከረ በኋላ፣ “ወደ ቄሳር ይግባኝ ስላልህ፣ ወደ ቄሳር ትሄዳለህ!” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያን ጊዜ ፊስጦስ ከአማካሪዎቹ ጋር ተነጋገረና “ወደ ሮማ ንጉሠ ነገሥት ይግባኝ ካልክ ወደ ንጉሠ ነገሥቱ ትሄዳለህ” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዚህም በኋላ ፊስጦስ ከአማካሪዎቹ ጋር ተማክሮ፥ “ወደ ቄሣር ይግባኝ ካልህ ወደ ቄሣር ትሄዳለህ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያን ጊዜ ፊስጦስ ከአማካሪዎቹ ጋር ተማክሮ፦ “ወደ ቄሳር ይግባኝ ብለሃል፤ ወደ ቄሳር ትሄዳለህ” ብሎ መለሰለት። |
ይህም በተፈጸመ ጊዜ ጳውሎስ “ወደዚያ ደርሼ ሮሜን ደግሞ አይ ዘንድ ይገባኛል፤” ብሎ በመቄዶንያና በአካይያ አልፎ ወደ ኢየሩሳሌም እንዲሄድ በመንፈስ አሰበ።
በሁለተኛውም ሌሊት ጌታ በአጠገቡ ቆሞ “ጳውሎስ ሆይ! በኢየሩሳሌም ስለ እኔ እንደ መሰከርህ እንዲሁ በሮሜም ትመሰክርልኝ ዘንድ ይገባሃልና አይዞህ፤” አለው።
እንግዲህ በድዬ ወይም ሞት የሚገባውን ነገር አድርጌ እንደሆነ ከሞት ልዳን አልልም፤ እነዚህ የሚከሱኝ ክስ ከንቱ እንደሆነ ግን ለእነርሱ አሳልፎ ይሰጠኝ ዘንድ ማንም አይችልም፤ ወደ ቄሣር ይግባኝ ብዬአለሁ፤” አለ።
ወደ ኢጣሊያም በመርከብ እንሄድ ዘንድ በተቆረጠ ጊዜ፥ ጳውሎስንና ሌሎችን እስረኞች ከአውግስጦስ ጭፍራ ለነበረ ዩልዮስ ለሚሉት ለመቶ አለቃ አሳልፈው ሰጡአቸው።
ይህ ናፍቆቴ ተስፋዬም ነውና፤ በምንም ዓይነት ነገር አላፍርም፤ ነገር ግን በሕይወት ብኖር ወይም ብሞት፥ ክርስቶስ እንደ ወትሮው እንዲሁ አሁንም በሥጋዬ ይከብራል ብዬ በሙሉ ድፍረት እናገራለሁ።