La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ሐዋርያት ሥራ 22:27 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የሻለቃውም ቀርቦ “አንተ ሮማዊ ነህን? ንገረኝ፤” አለው፤ እርሱም “አዎን” አለ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

አዛዡም ወደ ጳውሎስ ቀርቦ፣ “አንተ ሰው እስኪ ንገረኝ፤ ሮማዊ ነህን?” አለው። እርሱም፣ “አዎን፤ ነኝ” አለው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ስለዚህ አዛዡ ወደ ጳውሎስ ቀረብ አለና “እስቲ ንገረኝ፤ አንተ የሮም ዜጋ ነህን?” አለው፤ እርሱም “አዎ፥ ነኝ፤” አለ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የሻ​ለ​ቃ​ውም ወደ እርሱ ቀርቦ፥ “አንተ ሮማዊ ነህን? እስኪ ንገ​ረኝ” አለው፤ ጳው​ሎ​ስም፥ “አዎን” አለው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የሻለቃውም ቀርቦ፦ አንተ ሮማዊ ነህን? ንገረኝ አለው፤ እርሱም፦ አዎን አለ።

Ver Capítulo



ሐዋርያት ሥራ 22:27
4 Referencias Cruzadas  

እንግዲህ ወታደሮቹና አዛዣቸው፥ የአይሁድም ሎሌዎች ኢየሱስን ይዘው አሰሩት፤


በጠፈርም በገተሩት ጊዜ ጳውሎስ በአጠገቡ የቆመውን የመቶ አለቃ “የሮሜን ሰው ያለ ፍርድ ትገርፉ ዘንድ ተፈቅዶላችኋልን?” አለው።


የመቶ አለቃውም በሰማ ጊዜ ወደ ሻለቃው ቀርቦ “ይህ ሰው ሮማዊ ነውና ታደርገው ዘንድ ካለህ ተጠበቅ፤” ብሎ ነገረው።


የሻለቃውም መልሶ “እኔ ይህን ዜግነት በብዙ ገንዘብ አገኘሁት፤” አለ። ጳውሎስም “እኔ ግን በእርሷ ተወለድሁ፤” አለ።