ሐዋርያት ሥራ 22:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም ‘ፍጠን፤ ከኢየሩሳሌምም ቶሎ ውጣ፤ ስለ እኔ የምትመሰክረውን አይቀበሉህምና፤’ ሲለኝ አየሁት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጌታም ሲናገረኝ አየሁ፤ እርሱም አሁኑኑ፣ ‘ፈጥነህ ከኢየሩሳሌም ውጣ! ስለ እኔ የምትመሰክረውን አይቀበሉህምና’ አለኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጌታም ተገልጦልኝ ‘አንተ ስለ እኔ የምትሰጠውን ምስክርነት ስለማይቀበሉ ሳትዘገይ በፍጥነት ከኢየሩሳሌም ውጣ’ አለኝ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ‘ስለ እኔ የምትመሰክረውን ምስክርነት አይቀበሉህምና ከኢየሩሳሌም ፈጥነህ ውጣ’ ሲለኝ አየሁት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም፦ ፍጠን ከኢየሩሳሌምም ቶሎ ውጣ፥ ስለ እኔ የምትመሰክረውን አይቀበሉህምና ሲለኝ አየሁት። |
እንግዲህ ከጌታ ፊት የመጽናናት ዘመን እንድትመጣላችሁ አስቀድሞም ለእናንተ የመረጠውን ኢየሱስ ክርስቶስን እንዲልክላችሁ፥ ኀጢአታችሁ ይደመሰስ ዘንድ ንስሐ ግቡ፤ ተመለሱም።