ዕውሮችንም በማያውቁት መንገድ አመጣቸዋለሁ፤ በማያውቁትም ጎዳና እመራቸዋለሁ፤ በፊታቸውም ጨለማውን ብርሃን አደርጋለሁ፤ ጠማማውንም አቀናለሁ። ይህን አደርግላቸዋለሁ፥ አልተዋቸውም።
ሐዋርያት ሥራ 22:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያ ብርሃንም ክብር የተነሣ ማየት ባይሆንልኝ ከእኔ ጋር የነበሩት ሰዎች እጄን ይዘው እየመሩኝ ወደ ደማስቆ ደረስሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከብርሃኑም ጸዳል የተነሣ ዐይኔ ስለ ታወረ፣ ከእኔ ጋራ የነበሩት እጄን ይዘው እየመሩ ወደ ደማስቆ አደረሱኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከብርሃኑ ማንጸባረቅ የተነሣ ማየት ስላልቻልኩ አብረውኝ የነበሩት ሰዎች እጄን ይዘው እየመሩኝ ወደ ደማስቆ አደረሱኝ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዚያም በኋላ ከመብረቁ ነፀብራቅ የተነሣ ዐይኔን ታወርሁ፤ አብረውኝ የነበሩትም እየመሩኝ ወደ ደማስቆ ደረስሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከዚያ ብርሃንም ክብር የተነሣ ማየት ባይሆንልኝ ከእኔ ጋር የነበሩት ሰዎች እጄን ይዘው እየመሩኝ ወደ ደማስቆ ደረስሁ። |
ዕውሮችንም በማያውቁት መንገድ አመጣቸዋለሁ፤ በማያውቁትም ጎዳና እመራቸዋለሁ፤ በፊታቸውም ጨለማውን ብርሃን አደርጋለሁ፤ ጠማማውንም አቀናለሁ። ይህን አደርግላቸዋለሁ፥ አልተዋቸውም።
እንግዲህ ሰውነትህ ሁሉ በብርሃን የተመላ፥ ጨለማም የሆነ የአካል ክፍል የሌለው ከሆነ፥ መብራት በፀዳሉ ብርሃን እንደሚሰጥህ እንዲሁ ሰውነትህ ሁሉ በብርሃን የተመላ ይሆናል።”
አሁንም፥ እነሆ፥ የጌታ እጅ በአንተ ላይ ናት፤ ዕውርም ትሆናለህ እስከ ጊዜውም ፀሐይን አታይም፤” አለው። ያን ጊዜም ጭጋግና ጨለማ ወደቀበት፤ በእጁም የሚመራውን እየዞረ ፈለገ።