ስለዚህ ያንጊዜ ወደ አንተ ላክሁ፤ አንተም በመምጣትህ መልካም አድርገሃል። እንግዲህ አንተ ከእግዚአብሔር ዘንድ የታዘዝኸውን ሁሉ እንድንሰማ እኛ ሁላችን አሁን በእግዚአብሔር ፊት በዚህ አለን።”
ሐዋርያት ሥራ 22:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ‘ጌታ ሆይ! ምን ላድርግ?’ አልሁት። ጌታም ‘ተነሥተህ ወደ ደማስቆ ሂድና ታደርገው ዘንድ ስለ ታዘዘው ሁሉን በዚያ ይነግሩሃል፤’ አለኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እኔም፣ ‘ጌታ ሆይ፤ ምን ላድርግ?’ አልሁት። “ጌታም፣ ‘ተነሥተህ ወደ ደማስቆ ሂድ፤ በዚያም ልታደርገው የሚገባህ ሁሉ ይነገርሃል’ አለኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔም ‘ጌታ ሆይ! ምን ላድርግ?’ አልኩ። ጌታም ‘ተነሥተህ ወደ ደማስቆ ሂድ፤ ልታደርገው የሚገባህ ነገር ሁሉ እዚያ ይነገርሃል’ አለኝ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ‘አቤቱ፥ ጌታዬ ምን ላድርግ?’ አልሁ፤ ጌታም፦ ‘ተነሥና ወደ ደማስቆ ሂድ፤ ልታደርገው የሚገባህንም ሁሉ በዚያ ይነግሩሃል’ አለኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጌታ ሆይ፥ ምን ላድርግ? አልሁት። ጌታም፦ ተነሥተህ ወደ ደማስቆ ሂድና ታደርገው ዘንድ ስለ ታዘዘው ሁሉን በዚያ ይነግሩሃል አለኝ። |
ስለዚህ ያንጊዜ ወደ አንተ ላክሁ፤ አንተም በመምጣትህ መልካም አድርገሃል። እንግዲህ አንተ ከእግዚአብሔር ዘንድ የታዘዝኸውን ሁሉ እንድንሰማ እኛ ሁላችን አሁን በእግዚአብሔር ፊት በዚህ አለን።”
እየተንቀጠቀጠና እየተደነቀ “ጌታ ሆይ! ምን አደርግ ዘንድ ትወዳለህ?” አለው። ጌታም “ተነሥተህ ወደ ከተማ ግባና ታደርገው ዘንድ የሚያስፈልግህን ይነግሩሃል፤” አለው።