ሐዋርያት ሥራ 19:36 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህንም የሚክደው ከሌለ፥ ጸጥ እንድትሉና አንዳች በችኮላ እንዳታደርጉ ይገባል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ፣ ይህ ሐቅ የማይካድ እንደ መሆኑ መጠን፣ ልትረጋጉና አንዳች ነገር በጥድፊያ ከመፈጸም ልትቈጠቡ ይገባችኋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህን የሚክድ ማንም ስለሌለ ጸጥ እንድትሉና በችኰላ ክፉ ነገር ከማድረግ እንድትጠነቀቁ ይገባል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህም እርስዋን መቃወም የሚቻለው ያለ አይመስለኝም፤ አሁንም ይህን በጠብና በክርክር ሳይሆን በቀስታ ልናደርገው ይገባናል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይህንም የሚክደው ከሌለ፥ ጸጥ እንድትሉና አንዳች በችኮላ እንዳታደርጉ ይገባል። |
የከተማይቱም ጸሐፊ ሕዝቡን ጸጥ አሰኝቶ እንዲህ አለ “የኤፌሶን ሰዎች ሆይ! የኤፌሶን ከተማ ለታላቂቱ አርጤምስ ከሰማይም ለወረደው ጣዖትዋ የመቅደስ ጠባቂ መሆንዋን የማያውቅ ሰው ማን ነው?