ከተማውም በሙሉው ተደበላለቀ፤ የመቄዶንያም ሰዎች የጳውሎስን ጓደኞች ጋይዮስንና አርስጥሮኮስን ከእነርሱ ጋር ነጥቀው በአንድ ልብ ሆነው ወደ ጨዋታ ስፍራ ሮጡ።
ሐዋርያት ሥራ 19:32 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወዲያና ወዲህም እያሉ ይጮኹ ነበር፤ በጉባኤው ድብልቅልቅ ሆኖ የሚበልጡት ስንኳ ስለምን እንደተሰበሰቡ አላወቁም ነበርና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጉባኤውም ተበጣብጦ፣ አንዱ አንድ ነገር ሲናገር ሌላውም ሌላ እየተናገረ ይጯጯኽ ነበር፤ አብዛኛውም ሰው ለምን እዚያ እንደ ተሰበሰበ እንኳ አያውቅም ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሕዝቡ መካከል ታላቅ ሁከት ስለ ነበር አብዛኞቹ ለምን እንደ ተሰበሰቡ እንኳ አያውቁም ነበር፤ በዚህ ምክንያት አንዱ አንድ ነገር እያለ ሲጮኽ ሌላው ደግሞ ሌላ ነገር እያለ ይጮኽ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያም በጨዋታው ቦታ የነበሩ ሰዎች እየጮኹ ቈዩ፤ በሌላም ቋንቋ የሚጮሁ ነበሩ፤ በጉባኤው ታላቅ ድብልቅልቅ ሆኖ ነበርና፤ ከእነርሱ የሚበዙት ግን በምን ምክንያት እንደ ተሰበሰቡ አያውቁም ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወዲያና ወዲህም እያሉ ይጮኹ ነበር፤ በጉባኤው ድብልቅልቅ ሆኖ የሚበልጡት ስንኳ ስለ ምን እንደተሰበሰቡ አላወቁም ነበርና። |
ከተማውም በሙሉው ተደበላለቀ፤ የመቄዶንያም ሰዎች የጳውሎስን ጓደኞች ጋይዮስንና አርስጥሮኮስን ከእነርሱ ጋር ነጥቀው በአንድ ልብ ሆነው ወደ ጨዋታ ስፍራ ሮጡ።
ዛሬ ስለተደረገው ‘ሁከት ነው፤’ ሲሉ እንዳይከሱን ያስፈራልና፤ ስለዚህም ስብሰባ ምላሽ መስጠት አንችልም፤ ምክንያት የለምና።” ይህንም ብሎ ጉባኤውን ፈታው።
ሕዝቡም እኩሌቶቹ እንዲህ እኩሌቶቹም እንዲያ እያሉ ይጮኹ ነበር፤ ስለ ጫጫታውም እርግጡን ማወቅ ባልተቻለ ጊዜ፥ ወደ ወታደሮች ሰፈር ይወስዱት ዘንድ አዘዘ።