ሐዋርያት ሥራ 19:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ብር ሠሪ የሆነ ድሜጥሮስ የሚሉት አንድ ሰው የአርጤምስን ቤተ መቅደስ ምስሎች በብር እየሠራ ለአንጥረኞች እጅግ ትርፍ ያገኝ ነበርና፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ድሜጥሮስ የተባለ አንድ የብር አንጥረኛ የአርጤምስን ቤተ መቅደስ ምስሎች ከብር ቀጥቅጦ እየሠራ ለሠራተኞቹ የሚያስገኘው ገቢ ቀላል አልነበረም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንድ ድሜጥሮስ የሚባል ብር አንጥረኛ የአርጤሚስን ቤተ መቅደስ ምስል ከብር እየሠራ ለአንጥረኞች ብዙ ትርፍ ያስገኝ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያም ብር ሠሪ የሆነ ድሜጥሮስ የሚባል አንድ ሰው ነበር፤ ለአርጤምስም ከብር የቤተ መቅደስ ምስል ይሠራ ነበር፤ አንጥረኞችንም እያሠራ ብዙ ገንዘብ ይሰጣቸው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ብር ሠሪ የሆነ ድሜጥሮስ የሚሉት አንድ ሰው የአርጤምስን ቤተ መቅደስ ምስሎች በብር እየሠራ ለአንጥረኞች እጅግ ትርፍ ያገኝ ነበርና፤ |
ድሜጥሮስና ከእርሱ ጋር ያሉት አንጥረኞች ግን በሰው ላይ ነገር እንዳላቸው፥ የመፋረጃ ቀንና አገረ ገዢዎች አሉ፤ እርስ በርሳቸው ይምዋገቱ።