ሐዋርያት ሥራ 19:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ክፉው መንፈስ ግን መልሶ “ኢየሱስንስ አውቀዋለሁ፤ ጳውሎስንም አውቀዋለሁ፤ እናንተሳ እነማን ናችሁ?” አላቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ርኩስ መንፈሱም፣ “ኢየሱስን ዐውቀዋለሁ፤ ጳውሎስንም ዐውቀዋለሁ፤ እናንተ ግን እነማን ናችሁ?” አላቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን ርኩሱ መንፈስ “ኢየሱስን ዐውቃለሁ! ጳውሎስንም ዐውቃለሁ! ኧረ እናንተ እነማን ናችሁ?” አላቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያም ክፉ መንፈስ፥ “በኢየሱስ አምናለሁ፥ ጳውሎስንም አውቀዋለሁ፤ እንግዲህ እናንተ እነማን ናችሁ?” ብሎ መለሰላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ክፉው መንፈስ ግን መልሶ፦ ኢየሱስንስ አውቀዋለሁ ጳውሎስንም አውቀዋለሁ፤ እናንተሳ እነማን ናችሁ? አላቸው። |
እርሱም በተለያየ በሽታ የታመሙትን ብዙዎችን ፈወሰ፤ ብዙ አጋንንትም አወጣ፤ ነገር ግን አጋንንቱ የኢየሱስን ማንነት ያውቁ ስለ ነበር እንዲናገሩ አልፈቀደላቸውም።