አጋንንትንም እያወጡ ይዞሩ ከነበሩት አይሁድ አንዳንዶች “ጳውሎስ በሚሰብከው በኢየሱስ እናምላችኋለን፤” እያሉ ክፉዎች መናፍስት ባሉባቸው ላይ የጌታን የኢየሱስን ስም ይጠሩባቸው ዘንድ ሞከሩ።
ሐዋርያት ሥራ 19:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የካህናትም አለቃ ለሆነ አስቄዋ ለሚሉት ለአንድ አይሁዳዊ ይህን ያደረጉ ሰባት ልጆች ነበሩት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የአይሁዳዊው የካህናቱ አለቃ የአስቄዋ ሰባት ወንዶች ልጆችም ይህንኑ ያደርጉ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የአይሁድ ሊቀ ካህናት የሆነ የአስቄዋ ሰባት ልጆችም እንዲሁ ያደርጉ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኒህ እንዲህ ያደርጉ የነበሩትም የካህናቱ አለቃ የአይሁዳዊው የአስቂዋ ልጆች ናቸው፤ እነርሱም ሰባት ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የካህናትም አለቃ ለሆነ አስቄዋ ለሚሉት ለአንድ አይሁዳዊ ይህን ያደረጉ ሰባት ልጆች ነበሩት። |
አጋንንትንም እያወጡ ይዞሩ ከነበሩት አይሁድ አንዳንዶች “ጳውሎስ በሚሰብከው በኢየሱስ እናምላችኋለን፤” እያሉ ክፉዎች መናፍስት ባሉባቸው ላይ የጌታን የኢየሱስን ስም ይጠሩባቸው ዘንድ ሞከሩ።