ሐዋርያት ሥራ 17:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይዘውም “ይህ የምትናገረው አዲስ ትምህርት ምን እንደሆነ እናውቅ ዘንድ ይቻለናልን? በጆሮአችን እንግዳ ነገር ታሰማናለህና፤ እንግዲህ ይህ ነገር ምን እንደሆነ እናውቅ ዘንድ እንፈቅዳለን፤” ብለው አርዮስፋጎስ ወደ ተባለው ስፍራ ወሰዱት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይዘውም አርዮስፋጎስ ወደተባለው ስፍራ በመውሰድ እንዲህ አሉት፤ “አንተ የምታስተምረው ይህ አዲስ ትምህርት ምን እንደ ሆነ እንድናውቅ ትፈቅዳለህን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ጳውሎስን ይዘው አርዮስፋጎስ በተባለው ስፍራ ወደሚሰበሰበው ጉባኤ አመጡትና እንዲህ አሉት፤ “ይህ አንተ የምታስተምረው አዲስ ትምህርት ምን እንደ ሆነ ማወቅ እንችላለንን? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይዘውም አርዮስፋጎስ ወደሚባል ሸንጎ ወሰዱት፤ እንዲህም አሉት፥ “ይህን የምታስተምረውን አዲስ ትምህርት እናውቅ ዘንድ ይቻለናልን? እስቲ ንገረን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይዘውም፦ ይህ የምትናገረው አዲስ ትምህርት ምን እንደሆነ እናውቅ ዘንድ ይቻለናልን? በጆሮአችን እንግዳ ነገር ታሰማናለህና፤ እንግዲህ ይህ ነገር ምን እንደሆነ እናውቅ ዘንድ እንፈቅዳለን ብለው አርዮስፋጎስ ወደ ተባለው ስፍራ ወሰዱት። |
ሕዝቡ በሙሉ በመደነቅ፥ “ይህ ምንድነው? በሥልጣን ርኩሳን መናፍስትን ያዝዛል፤ እነርሱም ይታዘዙለታል፤ ይህ አዲስ ትምህርት ምንድነው?” እያሉ እርስ በርስ ተጠያየቁ።
አንዳንዶች ወንዶች ግን ተባብረው አመኑ፤ ከእነርሱ ደግሞ በአርዮስፋጎስ ያለው የፍርድ ቤት ፈራጅ ዲዮናስዮስ ደማሪስ የሚሉአትም አንዲት ሴት ሌሎችም ከእነርሱ ጋር ነበሩ።
ከጥቂት ቀንም በኋላ ፊልክስ አይሁዳዊት ከነበረች ድሩሲላ ከሚሉአት ከሚስቱ ጋር መጥቶ ጳውሎስን አስመጣ፤ በኢየሱስ ክርስቶስም ስለ ማመን የሚናገረውን ሰማው።