ሐዋርያት ሥራ 16:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ራእይም ለጳውሎስ በሌሊት ታየው፤ አንድ የመቄዶንያ ሰው “ወደ መቄዶንያ ተሻገርና እርዳን፤” እያለ ቆሞ ሲለምነው ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጳውሎስም ሌሊት በራእይ አንድ የመቄዶንያ ሰው ቆሞ፣ “ወደ መቄዶንያ ተሻግረህ ርዳን” ብሎ ሲለምነው አየ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እዚያ በሌሊት አንድ የመቄዶንያ ሰው ቆሞ “ወደ መቄዶንያ ተሻገርና እርዳን!” እያለ ሲለምነው ጳውሎስ በራእይ አየ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለጳውሎስም በሌሊት አንድ መቄዶናዊ ሰው ቁሞ፥ “ወደ እኛ ወደ መቄዶንያ ዕለፍና ርዳን” እያለ ሲማልደው በራእይ ተገለጸለት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ራእይም ለጳውሎስ በሌሊት ታየው፤ አንድ የመቄዶንያ ሰው፦ “ወደ መቄዶንያ ተሻገርና እርዳን” እያለ ቆሞ ሲለምነው ነበር። |
ቆርኔሌዎስም እንዲህ አለው “በዚች ሰዓት የዛሬ አራት ቀን የዘጠኝ ሰዓት ጸሎት በቤቴ እጸልይ ነበር፤ እነሆም፥ የሚያንጸባርቅ ልብስ የለበሰ ሰው በፊቴ ቆመና
ከዚያም ወደ ፊልጵስዩስ ደረስን፤ እርሷም የመቄዶንያ ከተማ ሆና የወረዳ ዋና ከተማና ቅኝ አገር ናት፤ በዚህችም ከተማ አንዳንድ ቀን እንቀመጥ ነበር።
ይህም በተፈጸመ ጊዜ ጳውሎስ “ወደዚያ ደርሼ ሮሜን ደግሞ አይ ዘንድ ይገባኛል፤” ብሎ በመቄዶንያና በአካይያ አልፎ ወደ ኢየሩሳሌም እንዲሄድ በመንፈስ አሰበ።
ከተማውም በሙሉው ተደበላለቀ፤ የመቄዶንያም ሰዎች የጳውሎስን ጓደኞች ጋይዮስንና አርስጥሮኮስን ከእነርሱ ጋር ነጥቀው በአንድ ልብ ሆነው ወደ ጨዋታ ስፍራ ሮጡ።
በእስያም ዳርቻ ወዳሉ ስፍራዎች ይሄድ ዘንድ ባለው በአድራሚጢስ መርከብ ገብተን ተነሣን፤ የመቄዶንያም ሰው የሆነ የተሰሎንቄው አርስጥሮኮስ ከእኛ ጋር ነበረ።
ልዳም ለኢዮጴ ቅርብ ናትና ደቀ መዛሙርት ጴጥሮስ በዚያ እንዳለ ሰምተው፥ ወደ እነርሱ ከመምጣት እንዳይዘገይ እየለመኑ ሁለት ሰዎች ወደ እርሱ ላኩ።
ከእናንተም ጋር እያለሁ በሚጎድለኝ ጊዜ፥ ከመቄዶንያ የመጡት ወንድሞች የጎደለኝን በሙሉ ስላሟሉልኝ፥ በማንም ላይ ሸክም አልሆንኩም፤ በማንኛውም መንገድ በእናንተ ላይ ሸክም እንዳልሆን ተጠንቅቄአለሁ፤ እጠነቀቅማለሁ።
ወደ መቄዶንያም በመጣን ጊዜ፥ በሁሉ ነገር መከራን ተቀበልን እንጂ ሰውነታችን ዕረፍት አልነበረውም፤ ከውጭ ጠብ ነበረ፤ ከውስጥ ደግሞ ፍርሃት ነበረብን።
በጎ ፈቃዳችሁን ስለማውቅ፤ በእናንተ ላይ የምመካበትን ምክንያት ለመቄዶንያ ሰዎች፥ “አካይያ ከአምና ጀምሮ ተዘጋጅቶአል፤” ብዬ ተናግሬለሁ፤ ቅንዐታችሁም ብዙዎችን አነሣሥቶአል።