La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ሐዋርያት ሥራ 16:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ጳውሎስ ይህ ከእርሱ ጋር ይወጣ ዘንድ ወደደ፤ በእነዚያም ስፍራዎች ስለ ነበሩ አይሁድ ይዞ ገረዘው፤ አባቱ የግሪክ ሰው እንደሆነ ሁሉ ያውቁ ነበርና።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ጳውሎስም ይህ ሰው ከርሱ ጋራ እንዲሄድ ፈለገ፤ ስለዚህ በዚያ አካባቢ በነበሩ አይሁድ ምክንያት ይዞ ገረዘው፤ እነዚህ አይሁድ በሙሉ የጢሞቴዎስ አባት የግሪክ ሰው እንደ ሆነ ያውቁ ነበርና።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ጳውሎስ ጢሞቴዎስን ይዞ መሄድ ስለ ፈለገ በዚያ ስፍራ በነበሩት አይሁድ ምክንያት እንዲገረዝ አደረገው፤ ይህንንም ያደረገው እነርሱ የጢሞቴዎስ አባት አረማዊ መሆኑን ያውቁ ስለ ነበረ ስለ እነርሱ ብሎ ነው።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ጳው​ሎ​ስም ከእ​ርሱ ጋር ይዞት ሊሄድ ወደደ፤ በዚ​ያም ሀገር ስለ አሉት አይ​ሁድ ወስዶ ገረ​ዘው፤ አባቱ አረ​ማዊ እንደ ነበረ ሁሉም ያውቁ ነበ​ርና።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ጳውሎስ ይህ ከእርሱ ጋር ይወጣ ዘንድ ወደደ፥ በእነዚያም ስፍራዎች ስለ ነበሩ አይሁድ ይዞ ገረዘው፤ አባቱ የግሪክ ሰው እንደ ሆነ ሁሉ ያውቁ ነበርና።

Ver Capítulo



ሐዋርያት ሥራ 16:3
10 Referencias Cruzadas  

ነገር ግን ከጣዖት ርኩሰትና ከዝሙት ከታነቀም ከደምም ይርቁ ዘንድ እንድንጽፍላቸው እቆርጣለሁ።


በርናባስም ማርቆስ የተባለውን ዮሐንስን ደግሞ ከእነርሱ ጋር ይወስድ ዘንድ አሰበ፤


ጳውሎስ ግን ሲላስን መረጠ፤ ወንድሞችም ለእግዚአብሔር ጸጋ አደራ ከሰጡት በኋላ ወጣ፤


መገረዝ ቢሆን አለመገረዝም ቢሆን ምንም ማለት አይደለም፤ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ መጠበቅ ነው እንጂ።


አይሁድንም ለመጥቀም ስል ከአይሁድ ጋር እንደ አይሁዳዊ ሆንሁ፤ ከሕግ በታች ያሉትን መጥቀም እንድችል፥ እኔ ራሴ ከሕግ በታች ሳልሆን፥ ከሕግ በታች ላሉት ከሕግ በታች እንዳለሁ ሆንኩ።


ነገር ግን ከእኔ ጋር የነበረው ቲቶ እንኳ፥ ግሪካዊ ቢሆንም እንዲገረዝ አልተገደደም፤


ጴጥሮስን ለተገረዙት ሐዋርያ እንዳደረገው፥ እኔንም ደግሞ ለአሕዛብ ሐዋርያ አድርጎኛል።


በፍቅር የሚሠራ እምነት እንጂ በክርስቶስ ኢየሱስ መገረዝ ወይም አለመገረዝ አይጠቅምም።


ነገር ግን ጢሞቴዎስ ልጅ ለአባቱ እንደሚያገለግል ከእኔ ጋር ሆኖ ለወንጌል በማገልገል መፈተኑን ታውቃላችሁ።