ሐዋርያት ሥራ 15:38 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጳውሎስ ግን ይህን ከእነርሱ ጋር ሊወስድ አልፈቀደም፤ ከእነርሱ ዘንድ ከጵንፍልያ ተለይቶ ነበርና፤ ወደ ሥራም ከእነርሱ ጋር አልመጣም ነበርና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጳውሎስ ግን እርሱን ይዞ ለመሄድ አልፈለገም፤ ምክንያቱም፣ ቀደም ሲል ማርቆስ ከእነርሱ ተለይቶ በጵንፍልያ ስለ ቀረ እና ወደ ሥራ ዐብሯቸው ስላልሄደ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጳውሎስ ግን ይህ ሰው ከእነርሱ ጋር እንዲሄድ አልፈቀደም፤ ያልፈቀደበትም ምክንያት እሱ በጵንፍልያ ከእነርሱ ተለይቶ ስለ ቀረና ወደ ሥራም ከእነርሱ ጋር ስላልሄደ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጳውሎስ ግን ከእነርሱ ጋር ሊወስደው አልፈቀደም፤ እነርሱ በጵንፍልያ ሳሉ ትቶአቸው ሄዶአልና፤ አብሮአቸውም ለሥራ አልመጣም ነበርና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጳውሎስ ግን ይህን ከእነርሱ ጋር ሊወስድ አልፈቀደም፥ ከእነርሱ ዘንድ ከጵንፍልያ ተለይቶ ነበርና፥ ወደ ሥራም ከእነርሱ ጋር አልመጣም ነበርና። |
በፍርግያም በጵንፍልያም በግብጽም በቀሬናም በኩል ባሉት በሊቢያ ወረዳዎች የምንኖር፥ በሮሜም የምንቀመጥ፥ አይሁድም ወደ ይሁዲነትም የገባን፥