ሐዋርያት ሥራ 11:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለመናገርም በጀመርሁ ጊዜ መንፈስ ቅዱስ ለእኛ ደግሞ በመጀመሪያ እንደ ወረደ ለእነርሱም ወረደላቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እኔም ገና መናገር ስጀምር፣ መንፈስ ቅዱስ በመጀመሪያ በእኛ ላይ እንደ ወረደ ሁሉ በእነርሱም ላይ ወረደ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔም መናገር በጀመርኩ ጊዜ መንፈስ ቅዱስ በመጀመሪያ በእኛ ላይ እንደ ወረደ ዐይነት በእነርሱ ላይ ወረደ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ላስተምራቸው በጀመርሁ ጊዜም ቀድሞ በእኛ ላይ እንደ ወረደ ሁሉ መንፈስ ቅዱስ በእነርሱም ላይ ወረደ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለመናገርም በጀመርሁ ጊዜ መንፈስ ቅዱስ ለእኛ ደግሞ በመጀመሪያ እንደ ወረደ ለእነርሱ ወረደላቸው። |