2 ጢሞቴዎስ 2:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለዚህም ወንጌል ስል መከራን እቀበላለሁ፥ እንደ ወንጀለኛም በሰንሰለት እስከመታሰር ደርሻለሁ፤ የእግዚአብሔር ቃል ግን አይታሰርም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለዚህም እንደ ወንጀለኛ እስከ መታሰር ድረስ መከራን እየተቀበልሁ ነው፤ የእግዚአብሔር ቃል ግን አይታሰርም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህም ወንጌል ምክንያት እንደ ወንጀለኛ በሰንሰለት ታስሬ መከራ እቀበላለሁ፤ የእግዚአብሔር ቃል ግን አይታሰርም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይህንም በመስበክ እንደ ክፉ አድራጊ እስክታሰር ድረስ መከራ እቀበላለሁ፤ የእግዚአብሔር ቃል ግን አይታሰርም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይህንም በመስበክ እንደ ክፉ አድራጊ እስክታሰር ድረስ መከራ እቀበላለሁ፥ የእግዚአብሔር ቃል ግን አይታሰርም። |
በእስራቴም ወንጌልንም መመከቻና መጽኛ በማድረግ ሁላችሁ ከእኔ ጋር በጸጋ ተካፋዮች ስለ ሆናችሁ፥ በልቤ ትኖራላችሁና ስለ ሁላችሁ ይህን ላስብ ይገባኛል።
ከእናንተ በመቄዶንያና በአካያ የጌታ ቃል ብቻ አልነበረም የተሰማው፥ ነገር ግን በሁሉ ስፍራ የተወራው በእግዚአብሔር ያላችሁ እምነትም ጭምር ነበር እንጂ፤ ስለዚህም እኛ ምንም መናገር አያስፈልገንም።
በዚህም ምክንያት ይህን መከራ ደግሞ እቀበላለሁ፤ ነገር ግን ያመንኩትን አውቃለሁና አላፍርበትም፤ የሰጠሁትንም አደራ እስከዚያ ቀን ድረስ ለመጠበቅ እንደሚችል እርግጠኛ ነኝ።
እንግዲህ ስለ ጌታችን ምስክርነት በመስጠት ወይም ስለ እርሱ በታሰርሁ በእኔ አትፈር ይልቁንም እንደ እግዚአብሔር ኃይል መጠን ስለ ወንጌል አብረኸኝ መከራን ተቀበል።
ምናልባት “ክፉ አድራጊዎች ናቸው” ብለው ቢያሙአችሁም እንኳ እግዚአብሔር በሚጎበኝበት ቀን፥ ስለሚመለከቱት ስለ መልካም ሥራችሁ እርሱን እንድያከብሩት በአሕዛብ መካከል ኑሮአችሁ መልካም ይሁን።
ነገር ግን በገርነትና በአክብሮት አድርጉት፤ በክርስቶስ ያላችሁን መልካም ጠባይ በመንቀፍ የሚናገሩ ሰዎች በሐሜታቸው እንዲያፍሩ መልካም ሕሊና ይኑራችሁ።
ማንም ከእናንተ መካከል እንደ ነፍሰ ገዳይ፥ ወይም እንደ ሌባ፥ ወይም እንደ ክፉ አድራጊ፥ ወይም በሌሎች ጉዳይ ጣልቃ እንደሚገባ ሆኖ መከራ የሚቀበል አይኑር።