La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ሳሙኤል 3:27 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

አበኔርም ወደ ኬብሮን በተመለሰ ጊዜ፥ ኢዮአብ ለብቻው የሚያነጋግረው በመምሰል ወደ ቅጽሩ በር ይዞት ሄደ፤ እዚያም የወንድሙን የአሣሄልን ደም ለመበቀል ሆዱ ላይ ወግቶ ገደለው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

አበኔር ወደ ኬብሮን በተመለሰ ጊዜ፣ ኢዮአብ በቈይታ የሚያነጋግረው በመምሰል ዞር አድርጎ ወደ ቅጽሩ በር ይዞት ሄደ፤ እዚያም የወንድሙን የአሣሄልን ደም ለመበቀል ሲል፣ ሆዱ ላይ ወግቶ ገደለው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

አበኔር ወደ ኬብሮን በደረሰ ጊዜ ኢዮአብ በግል ሊያነጋግረው የፈለገ በመምሰል ወደ ቅጽሩ በር ገለል አድርጎ ወሰደው፤ እዚያም ሆዱን ወግቶ ገደለው፤ ኢዮአብ ይህን ያደረገበት ምክንያት አበኔር ቀደም ብሎ ወንድሙን ዐሣሄልን ስለ ገደለበት ለመበቀል ነው።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

አበ​ኔ​ርም ወደ ኬብ​ሮን በተ​መ​ለሰ ጊዜ ኢዮ​አብ በበር ውስጥ በቈ​ይታ ይና​ገ​ረው ዘንድ ወደ አጠ​ገቡ ወሰ​ደው፤ በዚ​ያም ለወ​ን​ድሙ ለአ​ሣ​ሄል ደም ተበ​ቅሎ ወገ​ቡን መታው፤ ሞተም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

አበኔርም ወደ ኬብሮን በተመለሰ ጊዜ ኢዮአብ በበር ውስጥ በቆይታ ይናገረው ዘንድ ወደ አጠገቡ ወሰደው፥ በዚያም ለወንድሙ ለአሣሄል ደም ተበቅሎ ሆዱን መታው፥ ሞተም።

Ver Capítulo



2 ሳሙኤል 3:27
16 Referencias Cruzadas  

ከዚያም አቤሴሎም፥ “እምቢ ካልህ እሽ ወንድሜ አምኖን አብሮን ይሂድ” አለው። ንጉሡም፥ “አብሮህ የሚሄደው ለምንድን ነው?” ሲል ጠየቀው።


እናንተ የዐጥንቴ ፍላጭ፥ የሥጋዬ ቁራጭ ወንድሞቼ ናችሁ፤ ታዲያ ንጉሡን ለመመለስ እንዴት የመጨረሻ ሰዎች ትሆናላችሁ?’


ከዚያም ኢዮአብ ከዳዊት ፊት እንደ ወጣ፤ ወደ አበኔር መልክተኞች ላከ፤ መልክተኞቹም ከሲራ የውሃ ጉድጓድ አጠገብ መለሱት። ዳዊት ግን ይህን አላወቀም ነበር።


ዳዊት ይህን ነገር ቆይቶ በሰማ ጊዜ እንዲህ አለ፤ “እኔም ሆንሁ መንግሥቴ ከኔር ልጅ ከአበኔር ደም በጌታ ፊት ለዘለዓለም ንጹሕ ነን፤


የሳኦል ልጅ ኢያቡስቴ አበኔር በኬብሮን መሞቱን በሰማ ጊዜ ወኔ ከዳው፤ መላው እስራኤልም ተሸበረ።


አባቴ ዳዊት ሳያውቅ ኢዮአብ ስለ ገደላቸው ስለ እነዚያ ሰዎች ደም ጌታ ኢዮአብን ይቀጣዋል፤ ኢዮአብ ከእርሱ የተሻሉትን ሁለት ንጹሓን ሰዎች ገድሎአል፤ እነርሱም የእስራኤል ጦር አዛዥ አበኔርና የይሁዳ ጦር አዛዥ ዐማሣ ነበሩ።


“የጽሩያ ልጅ ኢዮአብ የእስራኤል ሕዝብ የጦር መሪዎች ከነበሩት በኔር ልጅ አበኔርና በይቴር ልጅ ዐማሣ ላይ ያደረገውን ታስታውሳለህ፤ ሁለት በጦርነት ጊዜ ላፈሰሱት ደም በቀል በሰላም ጊዜ እነርሱን ገድሎ የወገቡን መታጠቂያ የእግሩን ጫማ በደም በክሎ በእኔ ላይ ምን እንዳደረገ ታውቃለህ።


በገለዓድ ባለው በምናሴ ነገድ እኩሌታ ላይ የዘካርያስ ልጅ አዶ አለቃ ነበረ፤ በብንያም ላይ የአብኔር ልጅ የዕሢኤል አለቃ ነበረ፤


ጠላትነቱን በተንኰል የሚሸሽግ፥ ክፋቱ በጉባኤ መካከል ይገለጣል።


የናታንያም ልጅ እስማኤል ከእርሱም ጋር የነበሩት አሥሩ ሰዎች ተነሥተው የሳፋንን ልጅ የአኪቃምን ልጅ ጎዶልያስን በሰይፍ መቱ፥ የባቢሎንም ንጉሥ በአገሩ ላይ የሾመውን ገደሉ።


ደም ተበቃዩ ራሱ ነፍሰ ገዳዩን ይግደል፤ ባገኛው ጊዜ ይግደለው።


እስኪሞት ድረስ በጥላቻ ገፍትሮ ቢጥለው፥ ወይም ሸምቆ አንዳች ነገር ቢጥልበት፥


“‘በድብቅ ባልንጀራውን የሚገድል የተረገመ ይሁን!’ “ሕዝቡም ሁሉ፥ ‘አሜን!’ ይበል።