2 ሳሙኤል 22:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በመከራዬ ቀን መጡብኝ፤ ጌታ ግን ደገፈኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በመከራዬ ቀን መጡብኝ፤ እግዚአብሔር ግን ድጋፍ ሆነኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔ በተቸገርኩበት ጊዜ በጠላትነት ተነሡብኝ በመከራዬ ቀን መጡብኝ፤ እግዚአብሔር ግን ጠበቀኝ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በመከራዬ ቀን ደረሱብኝ፤ እግዚአብሔር ግን ደጋፊዬ ሆነ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በመከራዬ ቀን ደረሱብኝ፥ እግዚአብሔር ግን ደገፋዬ ሆነ። |
ከእናንተ ጌታን የሚፈራ፥ የአገልጋዩንም ቃል የሚሰማ፥ በጨለማም የሚሄድ፥ ብርሃንም የሌለው፥ ነገር ግን በጌታ ስም የሚታመን፥ በአምላኩም የሚደገፍ ማን ነው?