La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ሳሙኤል 21:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ገባዖናውያንም፥ “በእኛና በሳኦል ወይም በእኛና በቤቱ መካከል ያለው የብርና የወርቅ ጉዳይ አይደለም፥ እንዲሁም ከእስራኤል ማንንም ለመግደል መብት የለንም” ብለው መለሱለት። ዳዊትም፥ “ታዲያ ምን ላድርግላችሁ?” ሲል ጠየቃቸው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ገባዖናውያንም፣ “ከሳኦልም ሆነ ከቤተ ሰቡ ብር ወይም ወርቅ የመጠየቅ መብት የለንም፤ እንዲሁም ከእስራኤል ማንንም ለመግደል መብት የለንም” ብለው መለሱለት። ዳዊትም፣ “ታዲያ ምን ላድርግላችሁ?” ሲል ጠየቃቸው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እነርሱም “ከሳኦልና ከቤተሰቡ ጋር ያለን ጥል በብርና በወርቅ የሚገታ አይደለም፤ ከዚህም በቀር እኛ ከእስራኤል ወገን ማንንም መግደል አንፈልግም” ሲሉ መለሱለት። ዳዊትም “ታዲያ ምን እንዳደርግላችሁ ትፈልጋላችሁ?” ሲል ጠየቃቸው።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የገ​ባ​ዖን ሰዎ​ችም፥ “ከሳ​ኦ​ልና ከቤቱ ወርቅ ወይም ብር አን​ፈ​ል​ግም፤ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ወገን እኛ የም​ን​ገ​ድ​ለው የለም” አሉት።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የገባዖን ሰዎችም፦ በእኛና በሳኦል ወይም በእኛና በቤቱ መካከል ያለው የብርና የወርቅ ነገር አይደለም፥ ከእስራኤልም ወገን እኛ የምንገድለው የለም አሉት። እርሱም፦ የምትናገሩትን አደርግላችኋለሁ አለ።

Ver Capítulo



2 ሳሙኤል 21:4
5 Referencias Cruzadas  

እርሱም፦ “የምሰጥህ ምንድነው?” አለ። ያዕቆብም አለው፦ “ምንም አትስጠኝ፥ ይህንም ነገር ብታደርግልኝ እንደገና በጎችህን አበላለሁ እጠብቃለሁም።


ሞት የተፈረደበትን ነፍሰ ገዳዩንም ለማዳን የነፍስ ዋጋ አትቀበሉ፤ እርሱ ፈጽሞ ይገደል።


ታላቁ ካህን ሳይሞት ወደ ምድሩ እንዲመለስ ወደ መማፀኛው ከተማ ከሸሸው ሰው የነፍስ ዋጋ አትቀበሉ።